በድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የበጀት፣ ኢኮኖሚ ንግድና ኢንድስትሪ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮን የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የመውጫ ውይይት አካሂዷል።
በሪፖርቱም በበጀት አመቱ በከተማ እና በገጠር የስራ እድል ፈጠራ በግብርና በማህበራዊ እና በአገልግሎት ዘርፍ በተሰሩ ስራዎች አበረታች ለውጥ መመዝገቡ ተገልጿል።
በበጀት አመቱ ለ19 ሺ ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩ የተገለጸ ሲሆን 85 በመቶ ለወጣቶች ፣ ለሴቶች እንዲሁም አካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ ተገልጿል።
ቋሚ ኮሚቴው ለቢሮው የተሰጡ ግብረመልሶችን፣ በገጠር እና ከተማ የውክልና አወጣጥ መድረኮች ላይ የተነሱ የህዝብ ጥያቄዎች፣ የበጀት አመቱ መደበኛና የካፒታል ፕሮጀክቶች አፈፃፀም፣ ከክህሎት ልማትና ስራ ዕድል ፈጠራ ጋር ተያያዝነት ያላቸውን ተግባራት አፈፃፀም ያሉበትን ደረጃ፤ በዘርፉ ያሉ ተግዳሮቶች ላይ በቼክ ሊስቱ መሰረት ሰፋ ያለ ውይይት በማድረግ በአፈፃጸም ሂደት የታዩ ጠንካራ ጎኖች ተጠናክረው እንዲቀጥሉና በውስንነት የተለዩ ጉዳዮች መታረም እንዳለባቸው የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ ግብረ መልስ ሰጥቷል።
ቢሮው በተለያዩ የስራ ዘርፎች የስራ እድል መፍጠሩን፣ የኮሌጆች እና ኢንድስትሪዎች ግንኙነትን ማጠናከር እንዲሁም የክህሎት መር አጫጭር ስልጠናዎች ጨምሮ በአመቱ የታቀዱ ተግባራት የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገቡንና በዘርፉ በውስንነት የተለዩትን እንዲታረሙ ለማድረግ የቀጣይ በጀት አመት እቅድ ውስጥ እንዲካተቱ እና ከሁሉም የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር የተጀመረውን ቅንጅታዊ አሰራር አጠናክሮ በማስቀጠል በስፋትና በጥራት የክህሎት መርና የከተማና የገጠር ስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንዳለባቸው የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ አይናለም ተዘራ አቅጣጫ በመስጠት የ2017 በጀት አመት የማጠቃለያ ምዕራፍ የመስክ ምልከታውን አጠናቀዋል ።


