ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች ጋር የችግኝ ተከላ አካሄዱ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመትከል ማንሰራራት በሚል መርህ ዛሬ ማለዳ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብርን በመቀጠል፤ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች ጋር የችግኝ ተከላ አካሂደናል ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመትከል ማንሰራራት በሚል መርህ ዛሬ ማለዳ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብርን በመቀጠል፤ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች ጋር የችግኝ ተከላ አካሂደናል ብለዋል።
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሴሪል ራማፎሳ ከብሪክስ የብራዚል ጉባዔ ጎን ለጎን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር መክረዋል። ፕሬዝዳንቱ በኤክስ ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት “ሁሌም ወንድሜን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማግኘቴ ደስተኛ ነኝ” ብለዋል። በብራዚል ሪዮ ዲጄኔሮ በተካሄደው 17ኛው የብሪክስ ጉባኤ፤ የአፍሪካን ፍላጎት እና ሁለንተናዊ ጥቅም ለማሳደግ በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል።
አራተኛው ናፍቆት የድሬዳዋ ሳምንት ከሀምሌ 21 እስከ ሀምሌ 25/2017 ዓ.ም “ናፍቆት ድሬ ለድሬዳዋ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ሁነቶች ይከበራል። በዚህም በበዓሉ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ለመሳተፍ ከሰባት ልጆቹና ከባለቤቱ ጋር ከአስር አመታት የካናዳ ቆይታ በኋላ ወደ ድሬዳዋ የመጣው ሰሀል ሀርጌ ድሬዳዋ በከፍተኛ የልማት ግስጋሴ ላይ እንደምትገኝ መመልከቱን ገልጿል። አቶ ሰሀል የድሬዳዋ የአፈተኢሳ ሰፈር ልጅ ሲሆን…
የዓለም የኢኮናኖሚ ሥርዓት ለምዕራባውያን ያደላ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ይህንን የኢኮኖሚ ሥርዓት ሚዛናዊ ማድረግ ይገባል በሚል ነበር ብሪክስ እኤአ በ2006 የተመሠረተው፡፡ መስራቾቹ ደግሞ ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ህንድ እና ቻይና ሲሆኑ፣ ደቡብ አፍሪካ እኤአ በ2010 ጥምረቱን ተቀላቅላለች፡፡ ጥምረቱ የተመሰረተበት ዋና ዓላማ ተባብሮ በመስራት ሀገራቱ ኢኮኖሚያቸውን እንዲያሳድጉ ማድረግ ነው፡፡ የነዚህ ሀገራት ኢኮኖሚ በፍጥነት እያደገ በመምጣቱ ‘ታይገር ኤኮኖሚ’ የሚል ስያሜም አግኝቷል፡፡…
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ጋር በሪዮ ዴጄኔሮ ተገናኝተው በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ ኢትዮጵያ እና ቻይና በማንኛውም ሁኔታ የማይለያዩ ሁለንተናዊ ስትራቴጂካዊ አጋሮች መሆናቸውን እንደተናገሩ ሺንዋ ዘግቧል። ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር በኢኮኖሚ፣ በንግድ፣ በኢንዱስትሪ፣ በማዕድን፣ በኮሙኒኬሽን፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ በመሠረተ ልማት፣ በቱሪዝምና በሌሎችም ዘርፎች ያላትን ትብብር ለማጠናከር እንደምትፈልግ…
በድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የበጀት፣ ኢኮኖሚ ንግድና ኢንድስትሪ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮን የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የመውጫ ውይይት አካሂዷል። በሪፖርቱም በበጀት አመቱ በከተማ እና በገጠር የስራ እድል ፈጠራ በግብርና በማህበራዊ እና በአገልግሎት ዘርፍ በተሰሩ ስራዎች አበረታች ለውጥ መመዝገቡ ተገልጿል። በበጀት አመቱ ለ19 ሺ ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩ የተገለጸ…
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ብሪክስ ከጠንካራ አዲስ ሀሳብ ተነስቶ ለዓለም አቀፍ ለውጥ የሚሰራ ብርቱ ኃይል ወደመሆን ተሸጋግሯል፤አዳዲስ አባላት በመጨመራቸውም የጋራ ድምፃችን የበለጠ ይጠናከራል ሲሉ ገልጸዋል። አያይዘውም የጋራ ዓላማችን የበለጠ ይጠራል፤ አቅማችንም ይሰፋል ሲሉ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለጹት፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሪዮ ዲ ጄኒሮ እየተካሄደ በሚገኘው 17ኛው የብሪክስ ጉባዔ የሰላም፣ የጸጥታ እና ዓለም አቀፍ አመራር…