አራተኛው ናፍቆት የድሬዳዋ ሳምንት ከሀምሌ 21 እስከ ሀምሌ 25/2017 ዓ.ም “ናፍቆት ድሬ ለድሬዳዋ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ሁነቶች ይከበራል።
በዚህም በበዓሉ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ለመሳተፍ ከሰባት ልጆቹና ከባለቤቱ ጋር ከአስር አመታት የካናዳ ቆይታ በኋላ ወደ ድሬዳዋ የመጣው ሰሀል ሀርጌ ድሬዳዋ በከፍተኛ የልማት ግስጋሴ ላይ እንደምትገኝ መመልከቱን ገልጿል።
አቶ ሰሀል የድሬዳዋ የአፈተኢሳ ሰፈር ልጅ ሲሆን ሀጃሊ፣ለገሀሬ እንዲሁም ክርስቶስና አዲሱ ት/ ቤቶችም ትምህርቱን የተከታተለባቸው ናቸው።
አቶ ሰሀል በካናዳ ለአስር አመታት የቆየ ሲሆን በተለይም በካናዳ ከሚገኙ ዲያስፖራዎች ጋር በጋራ በመሰባሰብ በድሬዳዋ በኢንቨስትመንት ዘርፍ የመሰማራት ሀሳብ እንዳለው ይናገራል።
በመጨረሻም አቶ ሰሀል በመላው ዓለም ለሚገኙ የድሬዳዋ ልጆች፣ ተወላጆችና ደጋፊዎች በዘንድሮ የናፍቆት ድሬ በዓል ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፤ በአሉንም ኑ! በጋራ እናክብር በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።


