4ኛው ናፍቆት ድሬ አለም አቀፍ የድሬዳዋ ቀን በሚል ስያሜ ከዛሬው የመክፈቻ የእግር ጉዞ የብሄር ሄረሰቦች ባህል፣ ታሪክ፣ ቋንቋና የማንነት መገለጫዎች ላይ ትኩረት ያደረጉ ሲንፖዚየም፣ የስነ-ፅሑፍ ስራዎች፣ስፖርታዊ ውድድሮች የልማት ፕሮጀክቶች ጉብኝት እንዲሁም አብሮነትን በሚያጠናክሩ ሁነቶች ለቀጣይ 5 ቀናት ይከበራል።
ናፍቆት ድሬ የድሬዳዋ ተወላጆች እና ወዳጆችን ከመላው ዓለም በሰባሰብ ናፍቆታቸውን ወዳጅነታቸውን የሚያጠናክሩበት ከመሆኑም ባለፈ በአስተዳደሩ በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ተሳትፎ የሚያደርጉበት ነው።
ሰላም ለማ
ምስል:- አገኘው ሸዋረጋ


