ዛሬ ማለዳ ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ ከምድር ባቡር አደባባይ መነሻውን ያደረገ ስፖርታዊ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ተከትሎ የእግር ጉዞ በአስተዳደሩ የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎች ጉብኝት እንደዚሁም ባለፉት ሶስት ዓመታት የናፍቆት ድሬ ሳምንታት የነበሩ የበዓሉን አጠቃላይ ገፅታ የሚያስቃኝ የፎቶ አውደ ርዕይ እና የድሬ ጣፋጭና ባህላዊ ምግቦች ቅምሻ መርሐግብሮች ተከብሯል ።
የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ የተከበሩ አቶ ከር ጁሀርና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ አምባሳደር ፍጹም አረጋን ጨምሮ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የመጡ ዲያስፖራዎች እንደዚሁም የከተማው ነዋሪዎች መነሻውን ከድሬዳዋ ምግብ ኮምፕሌክስ አካባቢ አድርጎ እስከ ሺኒሌ ባደረገው የባቡር ጉዞ ላይ ተሳትፈዋል።


