የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር የአስተዳደሩ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ሰብዓዊ ተልዕኮ እንዲሳካ ላበረከቱት የላቀ አበርክቶ ዕውቅና ተሰጣቸው።

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሐር አስተዳደሩ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ሰብዓዊ ተልዕኮ እንዲሳካ ላበረከቱት የላቀ አበርክቶ ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ አበራ ቶላ ለድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከማህበሩ የበላይ ጠባቂ ፕሬዝዳንት አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ የተበረከተና አስተዳደሩ ለድሬዳዋ የቀይ መስቀል ላደረገው ድጋፍ የተዘጋጀውን እውቅና ማረጋገጫ አስረክበዋል ።

የአስተዳደሩ ከንቲባ ከድር ጁሀር ማህበሩ ለሰጣቸው እውቅና በአስተዳደሩ ሥም አመስግነው የቀይ መስቀል ማህበርን ለመደገፍና ለማገዝ አስተዳደሩ ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል ።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ አበራ ቶላ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ከተመሠረተ 90ኛ አመቱን ዘንድሮ እያከበረ መሆኑን ገልፀው በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አደጋዎች ሳቢያ የሚደርሰው ሰብዓዊ ጉዳት ለመከላከል በየክልሎችና በአስተዳደሩ የሚገኙ ቅርጫፎች በሚፈለገው ልክ እንዲቀሳቀሱ እና ወጪያቸውን በራሳቸው እንዲሸፈኑ ለማድረግ ማቀዳቸውን ገልፀዋል ለዚህም አስተዳደሩ ቅርንጫፉን ለማጠናከር የበጀት ድጋፍ በማድረጉ አመስግነዋል።

ፕሬዝዳንቱ አያይዘውም የአስተዳደሩን ቅርንጫፍ በቀጣይ ከሴክተር መስሪያ ቤቶች ጋር አቀናጅቶ በመስራት አቅም የመገንባትና የበጎ ፍቃደኞች አባላትን ቁጥር መጨመርን ያለመ ዕቅድ የያዙ መሆኑንም ገልጸዋል ።

በመድረኩ በኢትዮጰያ በቀይ መስቀል ማህበር የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የተሰሩ ስራዎች ሪፖርት በቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ ሀላፊ ወ/ሮ በሀር አደም አማካኝነት የቀረበ ሲሆን በመድረኩ የማህበሩ ከፍተኛ አመራሮች ሀላፊዎችና አባላቶች ተገኝተዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *