የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ለአቅመ ደካማ ወገኖች የሚውል ድጋፍ አደረጉ

” በጎነት ለኢትዮጲያ ከፍታ ” በሚል መሪ ሀሳብ በኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ድጋፍ አድርጊነት እንዲሁም በብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሴቶች ክንፍ አስተባባሪነት ወሰን ተሻጋሪ የክረምት ንቅናቄ በጎ ተግባር መርሀ-ግብር በዛሬው እለት ተካሂዷል ።

በመርሀ-ግብሩም የፅዳት ዘመቻ እንዲሁም የችግኝ ተከላ የተካሄደ ሲሆን የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍም ለአቅመ ደካማ ወገኖቻችን እንዲሁም ለተማሪዎች የሚሆኑ የተለያዩ ድጋፎችን በዛሬው እለት አድርገዋል ። በዚሁ መርሀ-ግብር ላይም በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀርቢ ቡህ በጎነት ለኢትዮጲያ ከፍታ በሚል መሪ ሀሳብ የወሰን ተሻጋሪ የክረምት ንቅናቄ በጎ ተግባርን ምክንያት በማድረግ የምእራብ ሀረርጌ አመራሮች በድሬዳዋ ድጋፍ ለማድረግ በመምጣታቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

ሴቶች ክንፍ በክረምት ወራት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት በርካታ ስራዎች እየሰሩ እንደሚገኝ የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የሴቶች ክንፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ ወ\ሮ ኢፍቱ አህመድ ተናግረው የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ በድሬዳዋ አስተዳደር በመገኘት ላደረጉት ድጋፍም ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

ሴቶች የተለያዩ በጎ ስራዎች ላይ በንቃት በመሳተፍ አርአያ መሆን እንዳለባት የድሬዳዋ አስተዳደር የሴቶች ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ የሆኑት ወ\ሮ ሁክሚያ መሀመድ ተናግረዋል ለዚህ ፕሮግራም መሳካት ድጋፍ ላደረጉም ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

የፍቅር የአንድነት እና የአብሮነት ተምሳሌት በሆነችው ትንሿ ኢትዮጲያ ድሬዳዋ በመምጣታቸው መደሰታቸውን በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት ወ\ሮ ሳሚያ አብደላ ገልፀው የበጎ ስራዎች በቀጣይም ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚደሚገባም ነው በእለቱ ያስታወቁት ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *