በአስተዳደሩ የመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር ሪፎርም ትግበራን ውጤታማ በማድረግ የብልፅግና ተምሳሌት የሆነች ድሬዳዋን እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።
ከሀገራዊ የሪፎርም አቅጣጫዎች መካከል አንዱ በሆነው የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ትግበራ እንደሀገር ዲጂታል ሲቪል ሰርቪስን ለመገንባትና የመንግስት ተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥ ቀልጣፋ፣ ጥራት ያለው፣ ፍትሐዊ እና ለሁሉም ዜጋ ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችሉ በርካታ ጥረቶች በመደረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ በዘርፉ የተጀመሩ ጥረቶች የሚሳኩ ስለመሆናቸው ማሳያ ይሆን ዘንድ በፌዴራል ደረጃ የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ኢንሼቲቭ የሆነው መሶብ ዲጂታል…


