አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ያከናወናቸውን አበረታች ስራዎች በቀጣይም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገለፀ

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት የ2017 ዓ.ም እቅድ አፈፃፀም ማጠቃለያ ሪፖርት እና የ2018 በጀት አመት እቅድ ዝግጅትን አስመልክቶ ከፈፃሚዎች ጋር እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ።

በዚህም በመድረኩ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት የመልካም አስተዳደርና የቅሬታ አፈታት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሰዓዳ አዋሌ በ2017 ዓ.ም የማህበረሰቡን ሁለንተናዊ የልማት ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ

እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት የተገልጋዮችን እርካታ የሚጨምሩ በርካታ ስራዎች መሰራታቸው ገልፀው፤በተቋሙ የተከናወኑ አበረታች ስራዎች በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥሉ አመላክተዋል።

ወ/ሮ ሰአዳ አያይዘውም አንዳንድ ክፍተት የታየባቸው ቦታዎች ላይ በቀጣይ በ2018 በጀት ዓመት በትኩረት እና በቅንጅት እንደሚሰራ ጠቁመዋል።

በተያያዘም የድሬዳዋ አስተዳደር ግንባታ ፍቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር ባለስልጣን የ2017 በጀት አመት ዕቅድ አፈፃፀምና የ2018 በጀት አመት ዕቅድ ላይ ከባለድርሻ አካላት እና ከተቋሙ ፈፃሚዎች ጋር ውይይት አድርጓል።

በውይይቱም በበጀት አመቱ የተከናወኑ ውጤታማ ስራዎችን ለማስቀጠል እንዲሁም አንዳንድ የተስተዋሉ ክፍተቶች ላይ በ2018 በጀት አመት ተተኩሮ እንደሚሰራ ከመግባባት ላይ ተደርሷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *