የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤትና ተጠሪ ተቋማት፣ የብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ አባላት የ2017 ዓ.ም የክረምት ወራት የበጐ ፈቃድ አገልግሎት መርሀግብር በ06 ወረዳ የፅዳት ዘመቻ አካሄዱ

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤትና ተጠሪ ተቋማት፣ የብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ አባላት የ2017 ዓ.ም የክረምት ወራት የበጐ ፈቃድ አገልግሎት መርሀግብር በ06 ወረዳ የፅዳት ዘመቻ አካሄዱ ።

በፅዳት ዘመቻው የሴፍቲኔት ሰራተኞች ፣ የድሬዳዋ አሰተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤትና ተጠሪ ተቋማት፣የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ አባላትና የወረዳው ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።

በፅዳት ዘመቻው ማጠቃለያ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ገበየሁ ጥላሁን ሁሉም ማህበረሰብ አካባቢውንና መንደሩን ካፀዳ ድሬዳዋ ውብና ፅዱ ትሆናለች ያሉ ሲሆን በተለይ በዚህ የክረምት ወቅት ወባ፣ ደንጊና ችኩንጉኒያ በሽታዎች የሚቀሰቀሱበት ወቅት እንደመሆኑ ሁሉም አካባቢውን በማፅዳት የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል ::

ከአካባቢ ፅዳት ዘመቻው ማጠቃላያ በኋላም በኮኔል ድልድይ የአሸዋ ወንዝ መውረጃ ዳርና ዳር የአርንጓዴ ልማት ላይ የተሰማሩትን ማህበራትና ወጣቶችን የከንቲባ ፅ/ቤት አመራሮች ተዘዋውረው ተመልክተዋል ::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *