የድሬዳዋ አስተዳደር ንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮና ተጠሪ ተቋማት የ2017 ዓ.ም የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በተለያዩ መርሀግብሮች አካሂደዋል ።
የ2017 የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በሀገር አቀፍ እንዲሁም በድሬዳዋ አስተዳደር በተለያዩ የድጋፍ ስራዎች እየተካሄደ ይገኛል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮና ተጠሪ ተቋማት በክረምት በጎፈቃድ አገልግሎትን የችግኝ ተከላ እና የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ የአቅመ ደካሞች የቤት እድሳት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እንዲሁም የንግድ፣ኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት ሀላፊ አቶ ሀርቢ ቡህ ተገኝተው አስጀምረዋል።
በመርሀግብሩ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ አብዲ ሙክታር ከህብረተሰቡ ጋር በጋራ በመቆም የተጀመሩ ስራዎችን ከግብ እንደሚያደርሱ ገልፀዋል።
ከዚህ በተጨማሪም ለአቅመ ደካሞች በሚደረገው የቤት እድሳት ስምንት ቤቶችን ለማደስ እቅድ የተየዘ ሲሆን በዛሬው እለት በወረዳ ሁለት እና በወረዳ ሠባት የሚገኙ አራት ቤቶችን በማፍረስ የመልሶ ግንባታ ሂደት ተጀምሯል።
ተቋሙ ቀደም ሲል የደም ልገሳ መርሀግብር ማከናወኑ ይታወሳል።


