‎ሀገርን የሚወድ ሁሉ በበጎ ፍቃድ እና በአረንጓዴ አሻራ ስራ ላይ በመሳተፍ የዜግነት ድርሻቸውን መወጣት ይገባል ሲሉ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ ጥሪ አቀረቡ።

‎በድሬዳዋ አስተዳደር ግንባታና ፍቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን ሰራተኞች እና የዘርፉ ባለሞያዎች የአረንጎዴ አሻራ መርሃ ግብር በማሪያም ትምህርት ቤት አከናውነዋል።

‎በዘንድሮው ክረምት የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር 7 መቶ ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል ታቀዶ እየተሰራ ነው። በድሬዳዋ አስተዳደር የዚሁ አንድ አካል የሆነው የክረምት አረንጓዴ አሻራ መርሃግብር በድሬዳዋ አስተዳደር ግንባታና ፍቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን ሰራተኞች እና የዘርፉ ባለሞያዎች እና ባለድርሻ አካላቶችን ባሳተፈ መልኩ 250 የሚሆኑ ለምግብነት የሚውሉ ችግኞችን የመትከል ተግባር ተከናውኗል።

‎በመርሃግብር ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ፅህፈት ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ገበየሁ ጥላሁን ሀገርን የሚወድ ሁሉ በበጎ ፍቃድ እና በአረንጓዴ አሻራ ስራ ላይ በመሳተፍ የዜግነት ድርሻቸውን መወጣት ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

‎የድሬዳዋ አስተዳደር ግንባታና ፍቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳሬክተር አቶ ኤፍሬም ግርማይ በበኩላቸው በአለም ላይ የሚስተዋለውን የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመቋቋም ኢትዮጵያ የጀመረችውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር “በመትከል ማንሰራራት” የባለሥልጣኑ ሰራተኞችና ከባለድርሻ አካላቶች ጋር በመሆን የድርሻችንን ተወጥተናል ሲሉ ተናግረዋል።

‎የወረዳ 3 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ምትኩ ሁነኛው በበኩላቸው ወረዳቸው በከተማዋ ማሃል የሚገኝ እና ታሪካዊ መንደሮች የሚገኙበት እንደመሆኑ መጠን የሚተከሉትን እንዲፀድቁ በባለቤትነት የሚንከባከቡ ተቋማት ማህበራትና ድርጅቶችን እንዲከታተሉ የሚያደርጉበት አሰራር መዘርጋታቸውን ተናግረዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *