በአስተዳደሩ የመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር ሪፎርም ትግበራን ውጤታማ በማድረግ የብልፅግና ተምሳሌት የሆነች ድሬዳዋን እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።

ከሀገራዊ የሪፎርም አቅጣጫዎች መካከል አንዱ በሆነው የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ትግበራ እንደሀገር ዲጂታል ሲቪል ሰርቪስን ለመገንባትና የመንግስት ተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥ ቀልጣፋ፣ ጥራት ያለው፣ ፍትሐዊ እና ለሁሉም ዜጋ ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችሉ በርካታ ጥረቶች በመደረግ ላይ ይገኛሉ፡፡

በዘርፉ የተጀመሩ ጥረቶች የሚሳኩ ስለመሆናቸው ማሳያ ይሆን ዘንድ በፌዴራል ደረጃ የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ኢንሼቲቭ የሆነው መሶብ ዲጂታል የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ተቋም ተገንብቶ ወደ አገልግሎት መግባቱ እና መሰል ማዕከላት በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በአጭረ ጊዜ ውስጥ ተገንብተው አገልግሎት እንዲሰጡ አቅጣጫ መቀመጡን ተከትሎ በርካታ ተግባራት በመከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡

የድሬዳዋ አስተዳደርም የተቀመጠውን ሀገራዊ አቅጣጫ መሰረት በማድረግ የመሶብ ድሬ ዲጂታል የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ተቋምን ለመገንባት እና አገልግሎት ለማስጀመር በአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ክቡር አቶ ሀርቢ ቡህ የሚመራ አብይ ኮሚቴ እና 4 ንዑሳን ኮሚቴዎች ተደራጅተው ወደ ስራ በመግባት ዘርፈብዙ ተግባራትን በማከናወን ላይ የሚገኙ ሲሆን በዛሬው እለትም ከተለያዩ የአስተዳደሩ እና የፌዴራል ተቋማት ለተመለመሉና ወደ ማዕከሉ ለሚገቡ ባለሞያዎች በተለያዩ ርዕሶች የቅድመ ስራ የአቅም ግንባታ ስልጠና መሰጠት ጀምሯል።

በመድረኩ ተገኝተው ስልጠናውን ያስጀመሩት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የንግድ ኢንጉስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም የመሶብ ድሬ ዲጂታል የአንድ ማዕከል አገልግሎት ግንባታ አስተባባሪ አብይ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ሀርቢ ቡህ ባስተላለፉት መልዕክት እንደሀገር ብሎም እንደ አስተዳደር ተግባራዊ በመደረግ ላይ የሚገኘው የመንግስት አግልግሎት እና አስተዳደር ሪፎርምን ውጤታማ ማድረግ በሌሎች ዘርፎች ለሚከናወኑ የሪፎርም ስራዎች ውጤታማነት መሰረት ከመሆኑም ባለፈ ሁለንተናዊ ብልፅግናዋ የተረጋገጠ ኢትዮጵያን ለመገንባትና ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ የተጣለብንን ታሪካዊ ኃላፊነት በሚገባ በመወጣት በሀገረመንግስት ግንባታ ውስጥ አሻራችንን እንዴናኖር የተሰጠን እደል መሆኑን ተረድተን ለተግባራዊነቱ መረባረብ ይጠበቅብናል ሲሉ ተናግረዋል።

የመሶብ ዲጂታል የአንድ ማዕከል አገልግሎት የመንግስት አግልግሎት እና አስተዳደር ሪፎርምን ውጤታማ ማድረግ የሚቻል ሰለመሆኑ አንዱና ዋንኛው ማሳያ በሞኑን የገለፁት አቶ ሀርቢ ቡህ በአስተዳደራችን ማዕከሉን ለመገንባት እና ወደ ስራ ለማስገባት በርካታ የዝግጅት ስራዎች በመሰራት ላይ መሆናቸውንና በአጭር ጊዜ ውስጥም ተጥናቆ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ጠቁመው ማዕከሉን ለመቀላቀልከተለያዩ የአስተዳደሩ እና የፌዴራል ተቋማት ተመልምለው የቅድመ ስራ የአቅም ግንባታ ስልጠና የሚወስዱ ባለሞያዎች የመጀመሪያዎቹ የድሬ መሶብ ዲጂታል የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ተቋም ሰራተኞች በመሆናቸው ኩራት ሊሰማቸው እንደሚገባና በዚህም በአስተዳደሩ የመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር ሪፎርም ትግበራን ውጤታማ በማድረግ የብልፅግና ተምሳሌት የሆነች ድሬዳዋን እውን ለማድረግ እየተደረገ ያለው ጥረት እንዲሳካ የተሰጣቸውን አደራ በፍፁም ኢትዮጵያዊነት እንዲወጡም መልዕታቸውን አሰተላልፈዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀይር ሀጂኑር በበኩላቸው በአስተዳደሩ ዲጂታል የመንግስት አገልግሎትን እውን በማድረግ ረገድ የመሶብ ድሬ ዲጂታል የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጨ ተቋም ግንባታ የማይተካ ሚና እንዳለው ገልፀው ተቋሙን የሚቀላቀሉ ባለሞያዎችም ከአስተዳደሩ ትልቅ ኃላፊነት የተሰጣቸው መሆኑን በመረዳት ለዲጂታል አገልግሎት ስርዓት ግንባታው ውጤታማነት የሚጠበቄባቸውን እንዲወጡና ስልጠናውንም በሚገባ እንዲከታተሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የአቅም ግንባታ ስጥጠናው “የመሶብ አገልግሎት ምንነት፣የደንበኞች አገልግሎትና እርካታ፣የመንግስት ተቋማት ፈጠራን ማዳበር፣የሲስተም ማልማትና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣የመሶብ ድሬ አንድ ማዕከል አገልግሎት ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት የሥነ-ምግባርና የተጠያቂነት መመሪያ” በሚሉ ርዕሶች ለተከታታይ 4 ቀናት የሚሰጥ ይሆናል።

ምንጭ።፦የድሬዳዋ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *