የ2018 ዓ.ም ዕቅድ ተገመገመ
የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ቤት የበጀት ኢኮኖሚ ንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የንግድ ኢንደስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮን የ2018 በጀት አመት እቅድ ገምግሟል።
በዚህም የቢሮው የ2018 በጀት አመት እቅድ ቀርቦ የተገመገመ ሲሆን ከቋሚ ኮሚቴ አባላቶች ለተነሱ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ላይ የቢሮው አመራሮች ማብራሪያ ሰተዋል።
ቢሮው የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ወቅት በውሰንነት የተለዩ እና በቋሚ ኮሚቴው የተሰጡ ግብረ_መልሶችን ፣ በውክልና አወጣጥ መድረኮች የተነሱ ጥያቄዎች ተካተው የታቀዱ ሲሆን በባለድርሻ አካላት ውይይት ተደርጎበት በቢሮው ማኔጅመንት ተገምግሞ በአንድ እቅድ አንድ ሪፓርት የቀረበ መሆኑ ነው የተገለፀው።
ቢሮው ባለፈው አመት በተለያዩ የስራ ዘርፎች ያስመዘገባቸው ውጤቶች የበለጠ ለማጠናከር ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሰራሮችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት እና በ2018 በጀት አመት እቅድ ላይ በውስንነት የተገመገሙ ጉዳዮች ተካተው ለቋሚ ኮሚቴው እንዲላክ የተከበሩ ወ/ሮ አይናለም ተዘራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል ።


