የወረዳ 3 አስተዳደር የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2018 በጀት አመት እቅድ ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ገመገመ
በተጠናቀቀው 2017 በጀት አመትም የወረዳው ህብረተሰብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ስራዎች መሠራታቸው ተገልጿል።
በወረዳው በስራ እድል ፈጠራ የኑሮውድነትን ለመቀነስ በቅዳሜ እና እሁድ ገበያ በከተማ ግብርና ምርትና ምርታማነት ከማሳደግ አንጻር የአካባቢውን ሰላም ና ጸጥታ ከማስፈን እንዲሁም የህዝቡን የመልማት የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ከመመለስ አንጻር ዘርፈ ብዙ ውጤቶች መመዝገባቸውን የወረዳው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ምትኩ ሁነኝው ገልጸዋል።
በቀጣይም ይህንን የመጡ ውጤቶችን በተጨማሪ ድሎች በማጀብ የሕዝብን ተጠቃሚነትና እርካታ ለማሳደግ የተጀመረው እንቅስቃሴ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ሀለፊው ተናግረዋል፡፡
በመድረኩም የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2018 በጀት አመት እቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።
የውይይቱ ተሳታፊዎችም በቀረበው ሪፖርት እና እቅድ ላይ የተለያዩ ሀሳቦችና ጥያቄዎች የተነሡ ሲሆን በተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ የወረዳው ኃላፊ አቶ ምትኩ ምላሽ ሰጥተዋል።


