“ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ” በሚል መሪ ሀሳብ የብልፅግና ፓርቲ ያለፉት ዓመታት ጉዞ እንዲሁም የቀጣይ ዓመታት የትኩረት መስኮች ላይ ያተኮረ የአቅም ግንባታ ስልጠና ለአስተዳደሩ አጠቃላይ አመራሮች ላለፍት አራት ቀናት ሲሰጥ ቆይቷል ።
በብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ለአስተዳደሩ አጠቃላይ አመራሮች የተዘጋጀው የምክክር መድረክ ቃል በተግባር የተገለጠበት የፓርቲው ያለፉት ዓመታት ጉዞ እንዲሁም በቀጣይ ስኬቶችን ለማስቀጠል ፣ ክፍተቶችን ለመሙላትና በእቅድ የተያዙ ስራዎችን የሕዝቡን የላቀ ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ በውጤታማነት መፈፀም የሚያስችል አቅም መፍጠሪያ መድረክ ነበር ።
በዛሬው እለትም ባለፍት ቀናት በቀረቡት ሰነዶች ላይ በቡድን ውይይት አስከትሎ ለሀይል መድረክ የሚሆኑ ጥያቄዎች ከየቡድኑ ተሰብስበው በብልፅግና ፓርቲ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ ክቡር አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ በኩል ማብራሪያ የተሰጠባቸው ሲሆን የ 2018 ዓ.ም የስራ አቅጣጫ ተሰጥቷል ።


