የተከናወኑ ውጤታማ ስራዎችን በቀጣይ በጀበት አስቀጥሎ ለመጓዝ እና የቀሩ ውስንነት የታየባቸው ተግባራትን ቆጥሮ በመለየት የተሻለ ስኬት ማስመዝገብ የሚያስችል የጋራ መግባቢያ ሰነድ መሆኑን ያነሱት የወረዳ አስተዳደሩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አቤል ምስራቅ፣ የፓርቲና የመንግስት እቅዶችን በጋራ ገምግመን የተግባባኔባቸውን ነጥቦች በቃልኪዳን ሰነድ ማስፈር ያስፈለገው የሚታይ ውጤት ለማስመዝገብና ተጠያቂነትን ለማስፈን ነው ብለዋል ።
የወረዳው ካቢኔ አባላትና የዘርፍ ፈጻሚዎች የወረዳው ምክር ቤት አፈጉባኤ በእማኝነት በተገኙበት የጋራ መግባቢያ ሰነዱን ተፈራርመዋል ።
ዋና ስራ አስፈጻሚው ይህ የተጀመረው የ2018 በጀት ዓመት የማንሰራራት ዓመት እንደመሆኑ የታቀዱ የልማትና የአስተዳደር ስራዎችን አቅምን አሟጦ በመስራት ለማሳካት ያለንን ቁርጠኝነት በዚህ የኪዳን ሰነድ የጋራ ፊርማችን እናረጋግጣለን ብለዋል።


