የድሬዳዋ አስተዳደር የግብርና ውሀ ማእድንና ኢነርጂ ቢሮ የገጠር ልማት ሴፍቲኔት በአምስት ምእራፍ የተሰሩ ስራዎች ዙሪያ የሚመክር ውይይት እንዲሁም የልምድ ልውውጥ በዛሬው እለት መጀመሩ ይታወሳል ። በጠዋቱ መርሀ-ግብርም በአምስት ምእራፍ የተሰሩ ስራዎች የቀረቡ ሲሆን በመቀጥልም የጉብኝት መርሀ-ግብር ተካሂዷል ።
ጉብኝቱም በልማታዊ ሴፍቲኔት በአፈር እና ውሀ ጥበቃ ስራ የተሰሩ ስራዎችን በዋሂል ክላስተር ሁሉልሞጆ ገጠር ቀበሌ እንዲሁም በአሰሊሶ ክላስተር ገንደሪጌ ገጠር ቀበሌ ተጎብኝተዋል ። በጉብኝቱም በአፈር እና ውሀ ጥበቃ ስራዎች የመጡ ለውጦች ፣ በመስኖ ውሀ ላይ የተሰሩ ስራዎች እንዲሁም የአርሶ አደሮች እርሻ ተጎብኝቷል ።
በአፈር እና ውሀ ጥበቃ ስራ እጅግ ውጤታማ የሆኑ ስራዎች ተሰርተው ማየታቸውን የኢ.ፌ.ድ.ሪ ግብርና ሚኒስቴር የምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት ወ\ሮ ስንታየው ደምሴ ተናግረው እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉም ነው ያስታወቁት ።


