በድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የወረዳ 04 አስተዳደር የህዝብ ተመራጮች ከመረጣቸው ህዝብ ጋር የህዝብ ውክልና መወጣት የውይይት መድረክ በጠዋቱ መርሃ-ግብር ያከናወኑ ሲሆን፤ በከሰዓት ውሎ ደግሞ በወረዳው የሚገኙ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
በዚህም የገንደ ቆሬ ፖሊስ ጣቢያንና ጤና ጣቢያን አጠቃላይ የስራ ሂደት የተመለከቱ ሲሆን ከተቋማቱ አመራሮች እና ሰራተኞች ጋርም በአጠቃለያ በተቋማቱ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ምክክር አርገዋል።
በመጨረሻም የወረዳው ተመራጮች ከወረዳው አመራሮች ጋር በመወያየት፤ በጥንካሬ የተስተዋሉ ስራዎች በቀጣይ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በውስንነት የታዩት ስራዎች ላይ ደግሞ በቀጣይ በትኩረት እንዲሰራና ሁሉም አካላት ተገቢውን ሚናቸውን እንዲወጡ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ ፕሮግራሙ ተጠናቋል ።


