“በሀገሪቱ እየተመዘገቡ ያሉ የልማት ስራዎች የኢትዮጵያን ብልጽግናን አይቀሬነት የሚያረጋግጡ ናቸው..” አቶ ብሩክ ፈለቀ የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር !ድሬዳዋ የብልጽግና ተምሳሌት በሚል መሪ ሀሳብ የፓርቲው ያለፉት ዓመታት ጉዞዎችና የቀጣይ ዓመታት የትኩረት መስኮች ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር መንግሰት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ፣ፋይናስ እና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ፣ ወጣቶች እና እስፖርት ኮሙሽን እንዲሁም የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ የብልጽግ ህብረት አባላት ጋር የውይይት መድረክ አካሄደዋል።

በመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ መድረክ የቢሮ ኃላፊ አቶ ብሩክ ፈለቀ እንደገለጹት ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት አመታት የነበሩትን ችግሮችን ወደ ድል በመቀየር ለማመን የሚከብዱ እና አለም የመሰከረላቸውን የልማት ውጤቶች በማስመዝገብ በችግር ውስጥ ጸንቶ መቆየት ብቻ ሳይሆን ችግሮችን ወደ ድል በመቀየር ውጤት ማስመዝገብ የቻለ ጠንካራ ፓርቲ መሆኑን ተናግረዋል።

በኢኮኖሚ በማህበራዊ በፖለቲካ ዘርፎች ሪፎርም በማድረግ የተመዘገቡት አንጸባራቂ ድሎች የኢትዮጵያን ብልጽግና አይቀሬነት የሚያረጋግጡ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

እንደ አስተዳደር የተጀመሩ ዘርፈ ብዙ ብልፅግናን የማረጋገጥ ጉዞ ስኬታማ እንዲሆን በፍጥነት እና በጥራት ተግባራትን በማከናወን የዜጎችን ህይወት ለመለወጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ሀላፊው አንስተዋል።

በውይይት መድረኩም በባለፉት አመታት ጉዞ ስኬቶች እና ያጋጠሙን ተግዳሮቶች ወደ እድል የተቀየሩበትእንዲሁም ፓርቲው ለወደፊት የሚሰራባቸውን የትኩረት መስኮች ላይ የተዘጋጀ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎባቸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *