በመድረኮቹ ላይ ባለፉ የለውጥ ዓመታት በፓርቲና በመንግስት ጠንካራ አመራር ሁለንተናዊ ብሔራዊ አቅምን በማጠናከር ከሀገር ውስጥና ከውጭ የተጋረጡ ፈተናዎችን በመቋቋም በርካታ አኩሪ ስኬቶች መቀዳጀት መቻሉን አጉልቶ ማሳየት እንደሚገባ ተገልጿል።
የምክክር መድረኩ የወረዳና የክላስተር ህብረት አባላት በሀገራዊ ቀጣይ የእድገት ጉዞ ላይ የጠራ ግንዛቤ የጨበጡበትና በሁሉም መስክ በሀገራዊ ለውጡ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ አቅም የፈጠሩበት ሆኗል።
ሲካሄድ በቆየው ውይይትም የድሬዳዋን የብልፅግና ተምሳሌትነት እንዲሁም የኢትዮጵያን የከፍታ ጉዞ ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል በቀጣይም የፓርቲያችንን አሻጋሪ እሳቤዎች በቁርጠኝነት ለመፈፀምና ለማስፈፀም ተግባቦት ተፈጥሯል።
የውይይት መድረኩ በነገው ዕለትም የሚቀጥል ይሆናል፡፡


