የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በአስተዳደሩ ለሚገኙ ተቋማት ቢሮዎች የህዝብ ግንኙነትና የሚዲያ ባለሞያዎች ዲጂታል ሚዲያ ለላቀ ተግባቦት በሚል መሪ ቃል በሐረር ከተማ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል

በየጊዜው እየዘመኑና ለአጠቃቀም ያላቸው ቅለትና ምቹነት በመላው አለም ሰፊ ተቀባይነትና ተወዳጅነትን በመቀዳጀት ዓለማቀፍ ገናን መደበኛ የሚዲያ ተቋማትን ሳይቀር ወደራሳቸው መሳብ የቻሉት የማህበራዊ ሚዲያዎች ያላቸውን ሰፊ የተደራሽነት ሽፋንና የተጽእኖ ፈጣሪነት አቅምን በመገንዘብ አብሮ መጓዝ የሚያስችል እውቀትና ክህሎት መጨበጥ ጊዜው የግድ የሚለው በመሆኑ ይህ ስልጠና መዘጋጀቱን ነው የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የመረጃ ማፍራት እና ማብቃት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እና የቢሮ ኃላፊ ተወካይ አቶ አቤል ሞላ የገለጹት።

እነዚህን ኢ መደበኛ የመገናኛ አውታሮች የይዘት፣ የአቀራረብና የአጠቃቀም ግንዛቤን በማሳደግ የመረጃ ምንጭ አማራጮችን በማስፋት አሁናዊ ሁነቶችና ክንውኖችን፣ ማህበራዊ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ርእሰ ጉዳዮችን ፈጣን፣ ቀልጣፋና ጥራት ባለው መንገድ እንደ አውዱ ለማሰናዳት የሚያስችል ስልጠና መሰጠቱ በተግባቦት ስራዎቻችን ላይ አወንታዊ ለውጥ እንድናመጣ የሚያግዝ ነው ሲሉ የስልጠናው ተሳታፊዎች ገልጸዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *