የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ለህዝብ ግንኙነትና የኮሚዩኒኬሽን ባለሞያዎች በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘመን ተግባቦት ላይ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ።
በዚህም የስልጠናው ተሳታፊዎች ያለንበትን የዲጂታል ዘመን የሚመጥን ስራዎችን ሰርተን በምን መልኩ ለማህበረሰቡ ማቅረብ እንዳለብን ከስልጠናው እውቀቶችን ጨብጠናል በማለት የተናገሩ ሲሆን፤ የኮሚዩኒኬሽን እና ሚዲያ ተቋማት የዲጂታል ዘመንን የሚመጥን ስራ ለመስራት ቅንጅታዊ አሰራርን ማሳደግ እንደሚገባቸውም አመላክተዋል።
ከህዝብ የሚነሱ የተለያዩ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ ከማድረግ ባሻገር የመረጃ ቅብብሎሽ ፈጣን እንዲሆን ለማድረግ መከናወን የሚገባቸው ስራዎች ላይ ግንዛቤ እንደጨበጡ ያብራሩት ሰልጣኞቹ፤ የሚዲያ እና ኮሙዩኒኬሽን ተቋማት ፈጣን፣ ወቅታዊ እና ተዓማኒ መረጃን ለህብረተሰቡ በማድረስ የማህበረሰቡን የመረጃ ፍላጎት ለማሟላት እንደነዚህ አይነት ጊዜውን ያማከሉ ስልጠናውዎች አስፈላጊ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በመጨረሻም የመድረኩ ተሳታፊዎች ከስልጠናው ያገኙትን ዕውቀት ወደ መጡበት ተቋም ሲመለሱ በተግባር እንደሚያውሉት አመላክተዋል።
በመድረኩ ማጠቃለያ የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ብሩክ ፈለቀ በቀጣይም ጊዜውን ያመከሉና የዲጂታል ሚዲያ ላይ ያለን እውቀት በከፍተኛ ደረጃ የሚያሳድጉ እንደነዚህ አይነት ስልጠናዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቁመዋል።
በመድረኩ የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም በቢሮው የለውጥ ስራዎች እና የመልካም አስተዳደር ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር በሆኑት አቶ ተስፋሚካኤል ኤርሚያስ ቀርቦ የተገመገመ ሲሆን የ2018 ዓ.ም እቅድ ኦረንቴሽንም ተሰቷል።


