ዲጂታል ድሬ የ 5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር ተካሄደ::

የዲጂታል ድሬ የ 5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በዛሬው እለት በድሬዳዋ አስተዳደር ተካሂዷል ። በሩጫ ውድድሩ ላይም አዲሱ የቼቼ መተግበሪያ አገልግሎት በሩጫ ውድድሩ ላይ ተሳታፊ ለሆኑ አካላትም ተዋውቋል ።

የዲጂታል ድሬ የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድሩን የዕለቱ የክብር እንግዳ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ ሀርቢ ቡህ እንዲሁም ከፍተኛ የአስተዳደሩ አመራሮች አስጀምረውታል ።

ቀደምት የስልጣኔ ከተማ የሆነችውን ድሬዳዋ የዲጂታል ስማርት ሲቲ ከተማ ለማድረግ የተጀመሩ የቴክኖሎጂ ስራዎች የኮሪደር ልማቱ አንዱ አመላካች እንቅስቃሴ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ካሊድ መሐመድ ተናግረው የዲጂታል ድሬ የሩጫ ውድድርም ስኬታማ እንደነበር አስታውቀዋል ።

የድሬዳዋ አስተዳደር የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ሀላፊ የሆኑት አቶ አብዱላዚዝ ሻፊ በበኩላቸው የሩጫ ውድድሩ ህብረተሰቡን እና ቴክኖሎጂውን የማስተዋወቅ አላማ እንዳለው ገልፀው ተቋማዊ አሰራርን በማዘመን ተገልጋዩ ህብረተሰብ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ወጥ በሆነ መንገድ አገልግሎት እንዲያገኝ እንደሚያስችላቸውም አስታውቀዋል።

በሩጫ ውድድሩ ላይም በተለያዩ ካታጎሪዎች ላሸነፉ ተወዳዳሪዎች ሜዳሊያ እንዲሁም ደግሞ ለውድድሩ መሳካት አስተዋፆ ላበረከቱ ተቋማት የእውቅና ሰርተፊኬት ከዕለቱ የክብር እንግዶች እጅ ተቀብለዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *