የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሙ ኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ለህዝብ ግንኙነትና የኮሚዩኒኬሽን ባለሞያዎች በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘመን ተግባቦት ላይ ስልጠና ሰጠ

በመንግስት ተቋማትና ሴክተሮች የህዝብ ግንኙነት እና የኮሙዩኒኬሽን ባለሞያዎች ዘመኑን የዋጀ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ተግባቦት እውቀትና ክህሎት በማሳደግ የህዝቡን የመረጃ ፍላጎት ማሟላት የሚያስችል አቅም ሊገነባ እንደሚገባ የድሬዳዋ አስተዳደሮ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ብሩክ ፈለቀ ገልጸዋል ::

ለተግባቦት ስራው የዲጂታል ቴክኖሎጂው መልካም እድል እና ተግዳሮትም በእኩል ደረጃ ይዞ መምጣቱን የገለጹት አቶ ብሩክ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሰው ሰራሽ አስተውሎት በእውነትና በሐሰት መካከል ያለውን ልዩነት መለየት እስኪያዳግት ድረስ የተሳሳተ መረጃን ፣ እውነታን ማዛባትና የሐሰት መረጃዎችን በስፋት በየማህበራዊ ሚዲያዎቹ እንድመለከት እያደረገ ይገኛል ብለዋል ።

ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎችን ለህዝብ ተደራሽ ከማድረግ አኳያ ይህ የዲጂታል ቴክኖሎጂ የተግባቦት ክህሎት ለተግባቦት ባለሞያው አይተኬ ሚና ያለው መሆኑንም የስልጠናው ተሳታፊዎች አንስተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *