በምስራቅ አጎራባች ክልሎች የጋራ መድረክ ላይ ለመካፈል በፌዴሬሽን ም/ቤት ም/አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ዛሀራ ኡመድ የተመራ ልኡካን ቡድን ድሬዳዋ ከተማ ገባ::

ልዑክ ቡድኑ የድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ በድሬዳዋ አስተዳደር ም/ቤት ም/አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ከሪማ አሊ ፣ በም/ቤቱ ጸሀፊ የተከበሩ አቶ ማርቆስ ባዩህ እና በም/ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የምስራቅ አጎራባች ክልሎች የጋራ መድረክ የክልል መንግስታትን ግንኙነትን ማጠናከር ዓላማ ያደረገ ሲሆን መድረኩ፤የፌዴራል ከፍተኛ አመራሮች እና የአጎራባች ክልሎቹ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በነገው እለት በድሬዳዋ እንደሚካሄድ ለማወቅ ተችሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *