የንግድ ሳምንቱን የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ክቡር አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ እና የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ካሳሁን ጎፌ እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በደማቅ ስነ-ስርዓት ተከፍቷል።
የንግድ ሳምንቱ ከነሐሴ 24-29/2017 ዓ.ም ድረስ አዲስ አበባ መገናኛ በጥራት መንደር ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው ቦታ የተለያዩ አምራች ኢንዱስትሪዎች ምርትና አገልግሎቶች ያስተዋውቃሉ።
በንግድ ሳምንቱ ላይ በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች ምርትና አገልግሎታቸውን በማስተዋወቅ የገበያ ትስስርን እንደሚፈጠርላቸው ተገልፆዋል ።
የንግድ ሳምንቱ አዲስ አበባ መገናኛ አካባቢ በሚገኘው በጥራት መንደር እየተካሄደ ይገኛል ።


