የአፍሪካ አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ሲሆን ከጉባኤው ጎን ለጎን፤ የጉባኤው ተሳታፊዎች ቀጠናዊ የከንቲቦች ፎረም አባላት የሰብሰሀራ አፍሪካ 4 መቶ ከተሞችን በመወከል የሰባት ከተሞች ከንቲቦች ድሬዳዋ በአየር ንብረት ለውጥ ሊከሰቱ የሚችሉ ጉዳቶችን በመከላከሉ ረገድ እንዲሁም በጎርፍ መከላከል እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን እና የካርበን ልቀት ስራ ላይ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ለመመልከት ማምሻውን ድሬዳዋ ከተማ ገብተዋል።
እንግዶቹ በቆይታቸው በነገው እለት ከድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ ጋር ውይይት የሚያደርጉ ሲሆን ናሽናል ሲሚንት ከአስተዳደሩ ጋር በመተባበር የኢነርጂ ምንጩን በባዮ ማስ ለመተካት እየሰራ የሚገኘውን ስራዎች ይጎበኛሉ በተጨማሪም የሰንካሳ(SUNCASA) ፕሮጀክትን ጨምሮ በአስተዳደሩ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን እንደሚጎበኙ ተመላክቷል።
ባጠቃላይም የእንግዶቹ ጉብኝት የእርስ በእርስ ትስስርን ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋፆ እንዳለው የተጠቆመ ሲሆን እንግዶቹ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚቆዩ ይሆናል።
እንግዶቹ ድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ፣ በካቢኔ አባላት እንዲሁም በአስተዳደሩ በየደረጃው በሚገኙ አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።


