የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ሴቶች ክንፍ ፅህፈት ቤት በአስተዳደሩ ከሚገኙ 38 ቱም የገጠር ቀበሌዎች ለተውጣጡ የአደረጃጀት ሰብሳቢዎች የ2017 በጀት አመት የስራ አፈፃፀምና የ2018 ዓ.ም እቅድ ኦረንቴሽን መድረክ አካሄደ።
በዚህም የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ሴቶች ክንፍ ፅ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ኢፍቱ አህመድ ከዚህ ቀደም መድረኩ በከተማ ከሚገኙ የሴቶች ክንፍ አመራር እና አባላት ጋር መከናወኑን በማስታወስ የገጠሩን ማህበረሰብም ተደራሽ ለማድረግ የዛሬው መድረክ መከናወኑን ጠቁመዋል።
ወ/ሮ ኢፍቱ አያይዘውም በ 2017 ዓ.ም በርካታ አበረታች ስራዎች በተለያዩ ዘርፎች መከናወናቸውን ጠቅሰው፤በፖለቲካው ዘርፍ የሴቶችን ተሳትፎ በማሳደግ አቅማቸውን የማጎልበት ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።
ሴቶች ከጠባቂነት ተላቀው በራሳቸው አቅም ፈጥረው በኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ዘርፍ አበረታች ተሳትፎ እያከናወኑ እንደሚገኙ ወ/ሮ ኢፍቱ ተናግረው፤ በተለይም የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በማሳደጉ ረገድ በሌማት ቱሩፋት እንዲሁም በግብርና ስራዎች ሴቶች ከጓሯቸው ምርቶችን አምርተው ከመጠቀም ባሻገር ለገበያም በማቅረብ ተጠቃሚ የሆኑበት ስራዎች በበጀት ዓመቱ መሰራታቸውን አብራርተዋል።
በመጨረሻም በ2017 በጀት ዓመት የተከናወኑ አበረታች ስራዎች በቀጣይም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ወ/ሮ ኢፍቱ አመላክተው አንዳንድ ውስንነት የታየባቸው ስራዎች ላይ ደግሞ በ2018 ዓ.ም በቅንጅት እንደሚሰራ አመላክተዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በቀረበው ሪፖርት እና እቅድ ላይ የተለያዩ ሀሳቦችና ጥያቄዎች በማንሳት ውይይት ተደርጎ መድረኩ ተጠናቋል።


