የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ለመውሊድ በዓል የእንኳን አደረሳቹ መልዕክታቸውን አስተላለፉ

ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር የ1 ሺ 500ኛው የነብዩ መሀመድ የመውሊድ በዓል የአብሮነት፤የይቅርታና የመተባበር እንዲሆን ለእምነቱ ተከታዮች በምሉ እንዲሆን ልባዊ ምኞታቸውን ገልፀዋል።

በዓሉን ስናከብር ነብዩ ሙሐመድ በእስልምና ሀይማኖት በነበራቸው አስተምህሮት መሰረት የሰው ልጆች ያለ ዘርና ሃይማኖት ልዩነት የምድር ፍጡራን ሁሉ እኩል መሆናቸውን አስተምረውናል፤ እኛም ዛሬ ይን በዓል የምናከብር የዕምነቱ ተከታዮች የነብዩ አስተምህሮት በመላበስና ተግባራዊ በማድረግ ልናከብር እንደሚገባ ክቡር ከንቲባ ገልፀዋል፡፡

የተቸገሩትን በመረዳት፣ የታመሙትን በመጠየቅ ያዘኑትን በማፅናናት እና የተቀደሱ ተግባራትን ሁሉ በማከናወን የምናሳልፈው በዓል እንዲሆን ከልብ እመኛለሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *