“የአስተዳደሩን ስላምና ጸጥታ ፍጹም አስተማማኝ በማድረግ እንዲሁም የአስተዳደሩን ተወዳዳሪነት በማሳደግ የኢትዮጵያን ዕድገትና ብልጽግና ወደ ከፍታ ለማሻገር በአዲሱ አመትም በርብርብ ይሰራል”

የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር

ጳጉሜ 1 የፅናት ቀን “ጽኑ መሠረት ብርቱ ሀገር” በሚል መሪ ቃል በድሬዳዋ አስተዳደር በድምቀት ተከበረ።

በመረሀ ግብሩም የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ለጳጉሜ አንድ የፅናት ቀን እንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን በማስተላለፍ፤ ኢትዮጲያ በዓለም ላይ የራሷን መንገድ በመከተል ልማቷንና እድገቷን እያረጋገጠች አዲስ ታሪክ እየፃፈች ያለች ሀገር መሆኗን ገልፀዋል።

ሀገራችን ባለፉት ሰባት የለውጥ አመታት ከውስጥ እና ከውጪ ፖለቲካዊ፣ ዲፕሎማሲያዊና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎችን በስፋት ያስተናገደች ቢሆንም ሁሉንም ተግዳሮቶች በድል ማለፏን ከንቲባ ከድር ተናግረዋል።

ከህዳሴው ግድባችን ጀምሮ የውስጥ የፖለቲካ አለመግባባቶቻችንና የሃሳብ ልዩነቶቻችን ሽፋን በማድረግ ሉአላዊነትታችንን ለመድፈርና የራሳቸውን ድብቅ ፍላጎት ለማስፈፀም ባንዳና ባዳዎች በስፋት የተረባረቡ ቢሆንም ባለፉት ዓመታት በጀመርነው ጠንካራ የፀጥታና ደህንነት ተቋም የመገንባት ትልማችንን በጎ ስኬቶችን ማስመዝገብ ችለናል ሲሉ ከንቲባ ከድር ጨምረው አብራርተዋል።

ሀገራችንን የባህር በር ባለቤት ለማድረግ ያስቀመጥነው ህልም እና ትልም ግቡን እንዲመታ እንደ አስተዳደር የምንሰራቸው ተግባራትም ሆነ የምናደርጋቸው ሁለንተናዊ እንቅስቃሴዎች አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉም ከንቲባ ከድር አመላክተዋል።

በመጨረሻም ሀገራዊ ፅናትን ለማስቀጠል በጋራ እንረባረብ በማለት ክቡር ከንቲባ ከድር ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *