ጷግሜ 2 የህብር ቀን ህብረብሔራዊ አንድነትን በሚያጠናክሩ ልዩ ልዩ ሁነቶች በአስተዳደሩ በድምቀት እየተከበረ ነዉ
ህብረብሔራዊነትን ማዕከል ያደረገ ወንድማማች እና እህትማማችነትን፤የመደጋገፍ የመረዳዳት እሴቶችን በሚጠናክሩ ሰው ተኮር የሆኑ ተግባራት፣ የፓናል ውይይት በማከናወን በአስተዳደሩ በድምቀት እየተከበረ ነዉ
በፓናል የውይይት መድረኩም የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ክቡር አቶ ሀርቢ ቡህ ፣ምክትል አፈጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ከሪማ አሊ የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የሀይማኖት አባቶች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።


