ጳጉሜ አንድ የፅናት ቀን “ፅኑ መሠረት፤ ብርቱ ሀገር ” በሚል መሪ ሃሳብ በድሬዳዋ አስተዳደር በወታደራዊ ትርኢቶች እና በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።
ኢትዮጵያ ሀገራችን ሉዓላዊነቷ ተጠብቆ እንዲትቆይ የአባቶቻችን ፅናት እንዲሁም ጀግናው መከላከያ ሰራዊት እና የጠቅላላው የሰላምና ጸጥታ አካላት አስተዋጽኦ እጅግ ከፍተኛ እንደሆነ የድሬዳዋ አስተዳደር ፍትህ ፀጥታና ህግ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱሰላም አህመድ በመግለፅ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በዓሉን ሲያከብሩ ያነጋገርናቸው ተሳታፊዎችም የዘንድሮው ጳጉሜ-1 “የጽናት ቀን” የምናከብረው የማንነታችን መገለጫ የሆነው ታላቁ ህዳሴ ግድብ ተጠናቆ ለመመረቅ በተዘጋጀበት ጊዜ በመሆኑ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶናል በማለት ስሜታቸውን ገልፀዋል።
ሀገራችን ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷ ተጠብቆ ጸንታ እንዲትቆይ የጀግና ልጆቿ ተጋድሎ ከፍተኛ እንደሆነ የገለፁት አስተያየት ሰጪዎቹ አሁን ላይ ሀገራችን የጀመረችውን የብልፅግና ግስጋሴ ተረባርበን ማፋጠን ይገባል ሲሉም ተናግረዋል።


