“በህብር በመቆማችን ፈተናዎችን አልፈን ሀገራዊ ሉዓላዊነትን በማስከበር ለድል በቅተናል… “ክቡር አቶ ሀርቢ ቡህ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ

በድሬዳዋ አስተዳደር ጷግሜ 2 “የህብር ቀን” ብዙሀነት የኢትዮጵያ ጌጥ በሚል መሪ ሀሳብ ህብረብሔራዊ አንድነትን በሚያጠናክሩ ልዩ ልዩ ሁነቶች በድምቀት ተከበረ።

በፓናል ውይይቱም የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ክቡር አቶ ሀርቢ ቡህ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት በባለፉት አመታት በህብር በመቆማችን ፈተናዎችን አልፈን ሀገራዊ ሉዓላዊነትን በማስከበር ለድል በቅተናል ብለዋል።

ከቅርብ አመታት ወዲህ ኢትዮጵያ ከግጭት ተላቃ ዘላቂ ሰላም ወደ ማጽናት ተሻጋግራለች ብለዋል።

ለዚህም ስኬት መብቃት በተደመረው እና በተጠናከረው ህብረብሄራዊ አንድነታችን ማረጋገጫ በሆነው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የምርቃት ዋዜማ ላይ መሆናችን ማሳያ መሆኑን አስረድተዋል።

የህዝቦች ህብረብሔራዊ አንድነት እንዲቀነቀን የውል ትርክት በመገንባት የኢትዮጵውያን ህብራዊ ገጽታ እንዲጎላ በማድረግ ሂደትም የሚዲያ እና የተግባቦት ስራዎች አበርክቶ ከፍተኛ መሆኑንም ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ አንስተዋል።

በውይይቱም የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ባህል ታሪክ ቋንቋ ስልጣኔ ላይ ያተኮረ ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።

ያነጋገርናቸው የበዓሉ ተሳታፊ እንደገለጹት የህብረ ብሄራዊነት መገለጫ በሆነው የህብር ቀን በዓል ላይ ተገኝተው እርስ በእርስ የባህል ታሪክ ልውውጥ ማድረጋችን አንድነታችንን ይበልጥ የሚጠናክር ነዉ ሲሉ ተናግረዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *