የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከድሬዳዋ አስተዳደር ጋር በጋራ በመሆን የድሬዳዋን የስማርት ሲቲ ጉዞ ለማፋጠን እንዲሁም በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎችን ማጠናከር በሚቻልባቸው ነጥቦች ላይ ለመመካከር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ የተመራ ልኡካን ቡድን ድሬዳዋ ከተማ ገብቷል።

ልኡክ ቡድኑ ድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ በድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር፣ በድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ እንዲሁም በመስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እና በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ድሬዳዋ ዲስትሪክት አመራሮች እና ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *