በድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን የ 2018 ዓ.ም የታክስ ንቅናቄ ማስጀመሪያ እንዲሁም በተሻሻለ የፌደራል ገቢ አዋጅ ቁጥር 1395 \ 2017 ዙሪያ በዛሬው እለት ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር ውይይት ተካሂዷል ።
በመርሀ-ግብሩ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር ግብር ለአንድ ሀገር እድገት እና ብልፅግና አይነተኛ አስተዋፆ እንዳለውና በተለይም ከግብር ከፋዩ ማህበረሰብ በሚሰበሰበው ገቢም በአስተዳደሩ ላይ የተለያዩ የልማት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረው ግብር ከፋዩ ማህበረሰብ በቀጣይም ግብራቸውን በወቅቱ በመክፈል ለከተማቸው እድገት እና ብልፅግና የራሳቸውን አስተዋፆ ማበርከት እንዳለባቸውም ነው ክቡር አቶ ከድር ጁሀር በእለቱ ያስታወቁት።
የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ባለፍት ጊዜያት አጠቃላይ ከግብር ጋር ተያይዞ በርካታ የግንዛቤ ማስጨበጫ እንዲሁም የንቅናቄ ስራዎች በስፋት ሲሰሩ መቆየታቸውን የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱሰላም መሀመድ ተናግረው በ 2018 በጀት አመትም ከዚህ ቀደም ሲሰሩ የነበሩት የግንዛቤ እና የንቅናቄ ስራዎች በይበልጥ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ነው ያስታወቁት ።
በእለቱም የፌደራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል የወጣ አዋጅ ቁጥር 1395 \ 2017 ዙሪያ ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይትም ተደርጎበታል።


