የኤስኦኤስ የህፃናት መንደር በድሬዳዋ ለ635 ህጻናት የትምህርት መረጃ ቍሳቁስ ደጋፍ አድርጓል።
በድጋፍ ስነስርአቱ ላይ የኤስኦኤስ የህፃናት መንደር የሎኬሽን ኘሮግራም ዳይሬክተር አቶ መሉቀን አስፋው እንዳሉት የተደረገው ድጋፍ የኤስኦኤስ ህጻናት ወንደር በድሬዳዋ አሰተዳደር ከተማ ሶስት ፕሮጀክቶች እንዳሉት ገልፀው ሁለቱ ፕሮጀክቶች ውሎና አዳራቸውን ጐዳና ላይ ያደረጉ ህጻናትን የሚደግፍ መሆኑን ገልዋል፡
ከዚህ ውስጥ የዛሬው ድጋፍ አንዱ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ አካል ጐዳተኞችን ህጻናት ትኩረት በማድረግ የሚተገበር መሆኑን ገልዋል። ዛሬ እነዚህ ሁለቱ ፕሮጀክት በትብብር ወደ ትምህርት ቤት ለመግባት ድጋፍ የሚያሻቸውን ህጻናት በማለየት ለ635 ተማሪዎች የትምህርት ቀሳቀስ ድጋፍ አድርገናል ብለዋል።
የትምህርት መጠነ ማቋረጥን በተለያዩ ችግሮች ምክንያት የሚያቆጡ ተማሪዎችን ትምህርቸው እንግሊሙ ያስችላልም ብለዋል ልጆች የተለያዩ ፍላጐቶች ስላላቸው ልጆችን ማዕከል የደረገ ድጋሮችን ማድረግ ትውልድን መግንባት ነው ሲሉ አቶ ሙሉቀን ገልፀዋል፡
በድጋፍ ስነስርአቱ ላይ የድሬዳዋ አሰተዳደር ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሃላፊ ወ/ሮ ሁክሚያ አህመድና ሌሎችም የአስተዳደሩ ሰፍተኛ አመራሮች በመገኘት ስጦታውን ለተማሪዎች አስረክበዋል።


