የግድቡ መጠናቀቅን አስመልክቶ” እምርታ እና ማንሰራራት” በሚል መሪ ሀሳብ ህዝባዊ የፓናል የውይይት መድረክ በዛሬው እለት ተካሂዷል።
በፓናል የውይይት መድረኩም የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር በንግግራቸው የህዳሴ ግድባችን ኢትዮጵያውያን በደምና በላብ ዋጋ የከፈልንበት የህብረ ብሄራዊ አንድነታችን ውል የመቻል ምሳሌ ነዉ ብለዋል።
የህዳሴ ግድባችን በወጀብ ውስጥ ሳንናወጥ፥ በቁርጥ ቀን በጽናት እንድንቆም ያደረገን የአንድነታችን ውል፥ የጥቁር ህዝቦች የመቻል ህያው ማሳያ ነው።
ግድቡ በኤሌክትሪክ ሀይል ዘርፍ የኢትዮጵውያን ብልጽግና መዳረሻ ከመሆንም በላይ የኢትዮጵያ የማንሰራራት ምልክት ነዉ ብለዋል።
ከንቲባ ከድር ጁሀር አክለውም የይቻላል መንፈስ፣ ወኔና ቁጭት በማስቀጠል የመንግስትን የትኩረት አቅጣጫዎችና በአስተዳደሩ ውስጥ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ከፊት ሆኖ በመደገፍና የብልጽግና እሳቤን በማስረፅ ሁለንተናዊ ብልፅግናን ማረጋገጥ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
በመድረኩም የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ለኢትዮጵያውያን የሚያስገኝውን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታን የሚያስቃኝ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎባቸዋል።
የፓናል ውይይት ተሳታፊዎች በበኩላቸው፥ በህዳሴው ግድብ መጠናቀቅ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው፥ ወደፊትም መንግስት ለሚጀምራቸው ሀገራዊ ፕሮጀክቶች የበኩላቸውን ድርሻ በትጋት እንደሚወጡ ገልፀዋል።


