የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ የመንግስት ሰራተኞች ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ።

“ከጂኦስትራቴጂክ ኩስመና ወደ ታደሰ ቁመና ፤ ወደ ተሻለ ሀገር!” በሚል ወቅታዊ ሀገራዊ ርዕስ የድሬዳዋ አስተዳደር ሴክተር፣ ወረዳና ክላስተር የብልፅግና ፓርቲ አባል ያልሆኑ የመንግስት ሰራተኞች የተሳተፉበት የውይይት መድረክ ተካሄደ።

በኢትዮጵያ የብዙ ውስብስብ ችግሮች ምንጭ ሆኖ ለቆየው የጂኦስትራቴጂካዊ ጉዳይ ፍትሀዊ የጋራ ተጠቃሚነትን በሚያረጋግጥ አግባብ እልባት ለመስጠትና የባህር በር ጥያቄዋ በጎ ምላሽ እንዲያገኝ ያልተቆራረጠ ሰላማዊና ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች እየተደረገ መሆኑን በዚህም ከጂኦስትራቴጂካዊ ኩስመና ወደ ታደሰ ቁመና ለመሸጋገርና የተሻለች ሀገርን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የመንግስት ሰራተኞች ሚና ከፍተኛ መሆኑን በመረዳት ለውጤታማነቱ የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ በመድረኮቹ ላይ መልዕክት ተላልፏል።

የመድረኮቹ ተሳታፊ የመንግስት ሰራተኞች ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታዎችን በንቃት በመከታተልና በቂ የሆነ መረጃን በመታጠቅ የኢትዮጵያን ብልፅግና ማየት የማይፈልጉ የውስጥና የውጭ ጠላቶቻችን የሚያደርጓቸውን እኩይ እንቅስቃሴዎች በመከታተል እውነትን መሰረት ባደረጉ ተጨባጭ መረጃዎች አጀንዳዎቻቸውን በማክሰም ለሀገራቸው ዘብ ሆነው እንደሚሰሩና በተሰማሩበት የስራ ዘርፍም ተገቢውን አገልግሎት ለህብረተሰቡ በመስጠትና ለሀገር የሚከፈል ማንኛውንም መስዋትነት ለመክፈል መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *