የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የሴክተር፣ የወረዳና የክላስተር ህብረቶች የ2018 አንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ለመገምገም ያለመ ድጋፋዊ ሱፐርቪዥን በማካሄድ ላይ ይገኛሉ፡

የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የሱፐርቪዥን ቡድን በትላንትናው ዕለት በጀመረው ድጋፋዊ ክትትል የአስተዳደሩ ሴክተር፣ ወረዳና ክላስተሮች የብልፅግና ፓርቲ ህብረቶችን የ2018 የአንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ድጋፋዊ ሱፐርቪዥን በማካሄድ ላይ ነው፡፡

በበጀት ዓመቱ የዝግጅት ምዕራፍ በህብረቶቹ የተከናወኑ የፓርቲ ስራዎችን የአፈፃፀም ደረጃ በመፈተሽ በትግበራ ምዕራፍ የተሻለ አፈፃፀምን ለማስመዝገብ ግብዓት የሚሆኑ ግብረ-መልሶች መስጠትን ዋነኛ ዓላማ አድርጎ በመካሄድ ላይ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የድጋፋዊ ሱፐርቪዥን አባላቱ በተዘጋጀው ቼክሊስት መሰረት የህብረቶቹን የ2018 የአንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም በዝርዝር የተመለከቱ ሲሆን ከቡድን አባላቱ ለተነሱ ጥያቄዎችም የህብረትና የቤተሰብ አመራሮች ሰፋ ያለ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተውባቸዋል፡፡

የድጋፋዊ ሱፐርቪዥን ቡድን አባላቱ የህብረቶች አጠቃላይ የአፈፃፀም ደረጃ ከጊዜ ወደጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን በመጠቆም በአፈፃፀም ሂደት የታዩ ጥንካሬዎችን በማስቀጠልና በግብረ መልስ የተሰጡ ክፍተቶችን የእቅድ አካል በማድረግ በ2018 በጀት ዓመት የትግበራ ምዕራፍ እንደ አስተዳደር ሁሉም የህብረትና የቤተሰብ አመራሮች እና አባላት ተቀናጅተው እንዲሰሩም አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡

የድጋፋዊ ሱፐርቪዥኑ በቀጣይም በቀሪ ሴክተር፣ ወረዳዎችና ክላስተሮች እስከ መስከረም 30/2018 የሚቀጥል ይሆናል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *