በስራ እድል ፈጠራና በስራ ፈጠራ አገልግሎት ዙሪያ ስልጠና መስጠት ተጀመረ::

የድሬዳዋ የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጄክት ምዕራፍ ሁለት በገጠር ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የአመራር በቡድን ክህሎት፣በስራ እድል ፈጠራና በስራ ፈጠራ አገልግሎት ዙሪያ የተዘጋጀ ስልጠና መሰጠት ተጀመረ፡፡ስልጠናው ከፌደራል ፕሮጀክት ዩኒት እና ከድሬዳዋ ስራና ክህሎት ቢሮ ለተውጣጡ ባለሞያዎች የሚሰጥ ነው።

በስልጠናው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት አቶ ኢሳም ሁሴን የቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻል ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ በአጭር ጊዜ ውስጥ የመጠጥ ውሃ፣የመንገድ ግንባታ ፣የገጠር ቁጠባ እና ብድር ማህበራት ማደራጀት ፣በስራ እድል ፈጠራ እና በግብርና ዘርፍ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል። ፕሮጀክቱ የመንግስት የልማት አቅጣጫ ከመደገፍ አንፃር በሌማት ቱሩፋት እና አረንጓዴ አሻራ ላይ ሰፊ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ተናግዋል

ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር ፈቺና ፋይዳቸው ላቅ ያሉ ስራዎን እየሰራ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

የዛሬው ስልጠና በመሰረታዊነት በዚህ የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግላቸው በአዲስ የሚመሰረቱ 40 ያህል ማህበራት የወረዳ አመራሮች ባለድርሻ አካላት ወደ ስራ ከመግባታቸው አስቀድሞ ስለአፈፃፀም ሂደቱ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ይህ ስልጠና መዘጋጀቱን አውስተዋል።

ዛሬ ስለ ስራ ፈጠራ አገልግሎት፣ የንግድ ስራ ዕቅድ ዝግጅት እና ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የተዘጋጀ መመሪያን በተመለከተ ግንዛቤ ተሰጥቷል።በግብርና እንዲሁም በሌሎች ከግብርና ዘርፍ ውጪ ባሉ የስራ ዕድሎች ላይ ተሰማርተው የሚደረግላቸውን ድጋፍ ለተገቢ ዓላማው በማዋል ኑሯቸውን የሚያሻሽሉበት ሁኔታ ይፈጠራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡LLRP2 የአርብቶ እና አርሶ አደር ማህበረሰብ የኑሮ ሁኔታን ማሻሻልና የምርትና ምርታማነት ማሳደግ ሂደቱን መደገፍ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል፡፡

በገጠር ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የአመራር፣በቡድን ክህሎት፣በስራ እድል ፈጠራና በስራ ፈጠራ አገልግሎት ዙሪያ በተዘጋጀው ስልጠና የስራ ክህሎት ቢሮ ባለሞያዎች ፣የወረዳ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሰራተኞች የወረዳ አስተባባሪዎ እና ባለሞያዎች በስልጠናው ላይ ተሳታፊ ሆነዋል ሲል ዘገባውን ያደረሰን የግብርና ውሀ መአድን እና ኢነርጂ ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *