“በድሬዳዋ አስተዳደር እየተከናወኑ የሚገኙ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች በህዝቡ ርብርብና በአመራር ቁርጠኝኘት የተገኙ ስኬቶች ናቸው”

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ መሠረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት

የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ መሠረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጋር በጋራ በመሆን በድሬዳዋ አስተዳደር እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

በዚህም በጉብኝቱ ኮንቬንሽን ማዕከልን፣ “መሶብ ድሬ” የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫን፣ የእመርታ ቤተ-መፅሀፍን፣ በራስ አቅም እየተገነቡ የሚገኙ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክትንና ሪልእስቴቶችን፣ ነፃ የንግድ ቀጠናን፣ ደረቅ ወደብን፣ አዲሱ ምድር ባቡርን እንዲሁም የድሬዳዋ ኢንተርናሽናል እስታዲየምን ተመልክተዋል።

ከጉብኝቱ በመቀጠል የቋሚ ኮሚቴው አባላት ከክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ እንዲሁም ከድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፈቲያ አደን እና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አርገዋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ መሠረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ፕሮፌሰር መሀመድ አብዶ የጉብኝቱ ዋነኛ ዓላማ በድሬዳዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ለማጎብኘት፣ ለማበረታታት እና ለመደገፍ መሆኑን ገልፀዋል።

የተከበሩ ፕሮፌሰር መሀመድ አያይዘውም ድሬዳዋ ለማህበረሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት በቁርጠኝነት እየሰራች እንደምትገኝ መመልከታቸውን ጠቅሰው፤ በአጠቃላይ በድሬዳዋ አስተዳደር እየተከናወኑ የሚገኙ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች በህዝቡ ርብርብና በአመራር ቁርጠኝኘት የተገኙ ስኬቶች መሆናቸውን ገልፀዋል።

የነዋሪዎች የቤት ችግርን ለመፍታትም በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የተናገሩት የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ በቀጣይም የተጀመሩ የልማት ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል ይገባቸዋል በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢው የተከበሩ ዶ/ር እሸቱ ተመስገን በበኩላቸው የድሬዳዋ በፍጥነት እያደጉ ከሚገኙ ከተሞች ውስጥ በቀደምትነት እንደምትጠቀስ ገልፀዋል።

በድሬዳዋ አስተዳደር እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች ከማህበረሰቡ ጋር በመቀናጀት እየተሰሩ እንደሚገኙ የተከበሩ ዶ/ር እሸቱ ጠቅሰው ማህበረሰቡም የልማቱ ተጠቀሚ እየሆነ እንደሚገኝ አመላክተዋል።

የኮንቬንሽን ሴንተርን በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ወደ አገልግሎት ለማስገባት ርብርብ እንደሚደረግ የተናገሩ የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ ዶ/ር እሸቱ

ድሬዳዋ ዓለም አቀፍ ኢንቨስተሮችን በከፍተኛ ደረጃ መሳብ የሚችል የልማት ግስጋሴ ላይ እንደምትገኝ አመላክተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *