በአስተዳደሩ 3ኛዉ ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ከመስከረም 30 ጀምሮ ይሰጣል.. የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ

በድሬዳዋ አሰተዳደር 3ኛዉ ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ከመስከረም 30 ጀምሮ እንደሚሰጥ የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ይሱፍ ሰኢድ በዛሬው እለት ለሚዲያ አካላት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቀዋል።

የልጅነት ልምሻ በሽታ(ፖሊዮ) መከላከያ ክትባት እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት ከመስከረም 30 ጀምሮ ለተከታታይ 4 ቀናት እንደሚሰጥ ኃላፊው አስታውቀዋል።

በክትባት ዘመቻውም በአስተዳደሩ 97,364 ህጻናትን ለመከተብ መታቀድን የገለጽት ኃላፊው ክትባቱ ቤት ለቤት በሚደረግ ጉብኝት ይሰጣል ብለዋል።

በዚህም የክትባት ዘመቻ መላው የአስተዳደሩ ነዋሪዎች፣ ወላጆች እና አሳዳጊዎች ህጻናቱን በማስከተብ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ሲሉም ኃላፊው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።

በዘመቻው ከፖሊዮ ክትባት በተጨማሪ መደበኛ የህፃናት ክትባት መውሰድ ጀምረው ያቋረጡ እና መደበኛ ክትባት ላልጀመሩ ህፃናትም መደበኛ ክትባት ለመስጠት ዝግጅት መደረጉን ኃላፊው አስገንዝበዋል።

የልጅነት ልምሻ በሽታ(ፖሊዮ) ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች በሆኑ ሕፃናት ላይ ከፍተኛ የመከሰት እድል ያለው በሽታ መሆኑን ጠቁመው በሽታውን በክትባት መከላከል እንደሚቻልም አስረድተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *