የማህበረሰቡን ችግር ፈቺ የሆኑ ስራዎች በተጠናከረ መልኩ እየተሰሩ እንደሚገኝ ተገለፀ

የድሬዳዋ አስተዳደር ንግድ፣ ኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮና ተጠሪ ተቋማት የብልፅግና ፓርቲ ህብረት አባላት የ2018 ዓ.ም አንደኛ ሩብ ዓመት ኮንፍረንስ በዛሬው ዕለት አካሄዱ።

በዚህም በመድረኩ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ንግድ፣ ኢንደስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አብዲ ሙክታር ባለፉት ሶስት ወራት እንደ ቢሮ ከኢንደስትሪ እና ከቱሪዝም ጋር ተያይዞ ሰፋፊ ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀው፤በተለይም የማህበረሰቡን ችግር ፈቺ የሆኑ ውጤታማ ስራዎች በተጠናከረ መልኩ እንደሚሰሩ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

የኑሮ ውድነትን የማቅለል ስራ በተጨማሪም ከገልግሎት አሰጣጥና ከማኒፋክቸሪንግ ኢንደስትሪ ጋር ተያይዞም ስራዎች በቅንጅት እየተከናወኑ እንደሚገኙ አቶ አብዲ ተናግረው 11 አዳዲስ ኢንደስትሪዎችን ወደ ስራ ማስገባት መቻሉንና ለዚህም የብልፅግና ፓርቲ ህብረት አባላቱ ሚና ጉልህ መሆኑን ገልፀዋል።

የተቋሙን የአገልግሎት አሰጣጥ ዲጂታላይዝ እና ቀልጣፋ የማረግ ስራ በተጠናከረ መልኩ እየተሰራ መሆነውን አቶ አብዲ አያይዘው ያነሱ ሲሆን ባለፉት ሶስት ወራት በክረምት የበጎ ፍቃድ ስራዎችም ማህበረሰቡን በከፍተኛ ሁኔታ የሚጠቅሙ ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል።

በመጨረሻም አቶ አብዲ የህብረቱ አባላቶች ቅንጅታዊ አሰራር ጠንካራ መሆኑን ገልፀው ይህም በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *