የድሬዳዋ አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት የማዘጋጃ ቤታዊ እና የሴክተር ተቋማት፤ የከተማ እና የገጠር ወረዳዎች የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ መድረክ በከሰዓቱ ውሎ የከተማ እና የገጠር ወረዳዎች የ2018 በጀት ዓመት የ 1ኛ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ በተገኙበት ተገምግሟል።
በዚህም በመድረኩ በአስተዳደሩ ፕላን እና ልማት ኮምሽን ከፍተኛ ባለሞያ በሆኑት አቶ ሀብታሙ ኪሮስ የከተማና የገጠር ወረዳዎች የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ከቤቱ ሀሳብ አስተያየት ተሰቶ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
በመጨረሻም ሁሉም ወረዳዎች የድሬዳዋን የኢንቨስትመንት እና የቱሪዝም ማእከልነት ለማጠናከር የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ፣ ቅንጅታዊ አሰራርን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚያስፈልግ፣ በወረዳዎች የአገልግሎት አሰጣጡን የማቀላጠፍ ሂደቱ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው፣ የኑሮ ውድነቱን የሚያባብሱ ህገ-ወጥ በሆነ መልኩ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ የቁጥጥር ስርአቱ መጠናከር እንደሚገባው፣ የከተማዋን ፅዳት እና ውበት ሊያበላሹ የሚችሉ በየመንገድ ዳር የሚከናወኑ ተግባራትን ማሶገድ እንደሚገባ እንዲሁም ሮንድን ማጠናከር እንደማገባ እና በሌሎችም ሀሳቦች ላይ ክቡር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።


