የአረንጓዴ ኢነርጂ አስተባባሪ ኮሚቴ ልኡክ በድሬዳዋ አስተዳደር በአድራ ኢትዮጵያ ፕሮጀክት የተሰሩ ስራዎች ላይ የልምድ ልውውጥ መድረክ አካሂዷል።
ልኡኩ በድሬዳዋ በአድራ ኢትዮጵያ (ADRA Ethiopia) ፕሮጀክት እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎች ላይ የልምድ ልውውጥ መድረክ ያካሄደ ሲሆን በSolar PV Instalation የተመረቁ ሰልጣኞች የስራ ምችችት ላይ እንዲሁም በአጠቃላይ በፕሮጀክቱ የተሰሩ ስራዎች ላይ ውይይት አድርጓል።
በዚህም በመድረኩ የተገኙት ኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ አድራ ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ድሬዳዋ መተግበር ከጀመረ 3 አመታት ማስቆጠሩን ገልፀው፤ በፕሮጀክቱ በተሰሩት ስራዎች በርካታ ወጣቶችን የስራ ባለቤት ማድረግ እየተቻለ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
አቶ ታደለ አያይዘውም በሶላር ፒቪ እና ኢኒስታሌሽን ዘርፍ የተመረቁ ወጣቶችን ወደ ስራ ለማስገባት በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
የADRA ፕሮጀክት ፕሮግራም ኮርዲኔተር አቶ ብስራት አበራ በበኩላቸው በድሬዳዋ በአድራ ኢትዮጵያ ፕሮጀክት የግሪን ኢነርጂ እስትሪም ኮሚቴ ስራዎች አበረታች መሆናቸው ገልፀዋል።
አቶ ብስራት አያይዘውም በተለይም በፕሮጀክቱ በድሬዳዋ በሚገኙ የገጠር አካባቢዎች የተሰሩ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው ጠቁመዋል።
የአድራ ኢትዮጰያ ፕሮጀክት የድሬዳዋ ፊልድ ኦፊስ ፕሮጀክት ማናጀር የሆኑት አቶ ሀብታሙ በየነ በአስተዳደሩ በሶላር ኢነርጂ ዘርፍ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ ገልፀው ይህም በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል።


