የድሬደዋ አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ አመት የማዘጋጃ ቤታዊ፤የሴክተር መስሪያ ቤቶች፤ የከተማ ቀበሌዎችና የገጠር ክላስተሮች የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ መድረክ አካሄዷል፡፡
በጠዋቱ ጊዜ በተካሄደው የግምገማ መድረክ የሴክተር መስሪያ ቤቶች የመጀመሪያ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም የአስተዳደሩ የፕላንና ኢኮኖሚ ልማት ኮሚሽን ኃላፊ በአቶ ኃይለማርያም ዳዲ አማካኝነት ቀርቧል።
በእቅድ አፈጻጸም የግምገማ መድረኩ የአስተዳደሩ የሱፓር ቪዥን ቡድን በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ እና በፍትህና መልካም አስተዳደር ዘርፍ በተቋማት ባካሄዱት ምልከታ በእቅድ አፈፃፀማቸው የተመለከቱትን ጠንካራና መስተካከል ያለባቸውን ክፍተቶችን አቅርበዋል።
በግምገማ መድረኩም ከተሳታፊዋች በቀጣይ ሊስተካከሉ የሚገባቸው ጉዳዮች የተነሱ ሲሆን የንሮ ውድነቱን የቅዳሜ እና እሁድ ገበያ ፣የአስተዳደሩ ገቢ አሰባሰብ ከማሳደግ አንፃር ፣በግብርናው ዘርፍ የእንሰሳት ተዋፅኦ ከማቅረብ፣ ፉብሪካዋች በልማት ስራው ያላቸው ውስንነቶች ዙሪያ ላይ ሀሳብና አስተያየቶች ሰተዋል።
የሪፖርት ግምገማ መድረኩን የመሩት የአስተዳደሩ ከንቲባ የተከበሩ ከድር ጆሀር በመድረኩ ላይ በቀረቡት የሴክተር ተቋማት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን በአጠቃላይ በመዳሰስ በቀጣይ መሻሻል ያለባቸውን በዝርዝር በማስቀመጥ ተቋማትን የሚመሩ አመራሮች እንደክፍተት ከቤቱ እና ከመድረኩ የተነሱ ክፍተቶችን በመውሰድ የተሻለ አፈፃፀም እንዲኖራቸው የስራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
ክቡር ከንቲባው አክለውም የአስተዳደሩን ገቢ ለማሳደግ እየተሰሩ ያሉ ስራዋች ጥሩ መሆናቸውን በመጠቆም ከአስተዳደሩ መሰብሰብ ያለበት ገቢ እንደሚቀረው ጠቁመው በቀጣይ ያልተነኩ እና ያሉትም የግብር ከፋዮች በአግባቡ የሚጠበቅባቸውን እንዲከፍሉ መደረግ እንዳለበት ገልፀዋል።
የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ በበኩላቸው የመልካም አስተዳደር በኩል ያሉ ችግሮችን ከመፍታት አኳያ፣ የንሮ ውድነትን አስመልክቶ የቅዳሜና እሁድ ገበያ እና የገበያ ቁጥጥሩ ስራ ተጠናክሮ መሰራት እንዳለበት በመግለፅ አገልጋይ መሪ ሆነን ስራዎችን መስራት ይገባል ብለዋል።


