በፈረንሳይ ሌጉ ከተማ ከንቲባ ሊዮኒዳስ ሰርጅ የተመራ 11 አባላትን የያዘ ልዑካን ቡድን የድሬዳዋን እና የሌጉ ከተማን እህትማማችነት ለማጠናከር ድሬዳዋ ከተማ ገባ
ድሬዳዋ እና የፈረንሳይዋ ሌጉ ከተማ እህትማማች ከተሞች ሲሆኑ በትምህርት፣ በጤና እና በሌሎችም ማህበራዊ ጉዳዮች አብሮ ለመስራት ስምምነት ተፈራርመዋል። ታዲያ ልዑክ ቡድኑ ወደ ድሬዳዋ የመጣበት ዋነኛ ምክንያት እህትማማች ከተማነትን ለማጠናከር እንዲሁም በድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ሀሳብ አመንጪነት ልዑክ ቡድኑ በድሬዳዋ ያሉ ምቹ ሁኔታዎችን በመመልከት በተለያዩ ዘርፎች ተሰማርቶ አብሮ ለመስራት በሚቻልባቸው ነጥቦች ላይ ለመምከር…


