“የመደመር ትውልድ ግንባታ ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ሀሳብ በወጣቶች እና በሴቶች ክንፍ ስር ለሚገኙ ግንባር ቀደም ወጣቶች ሴቶች የተዘጋጀ የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ነው።
ስልጠናው በዋናነት ሀገሪቱ የጀመረችውን የማንሰራራት ጉዞ በመረዳት የምትመሰል ሀገር ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ወጣቶች ሴቶች የዚህ ትውልድ አካል በመሆናቸው አቅሞቻቸውን ተጠቅመው በሀገር ግንባታ ሂደት አሻራ እንዲያኖሩ ግንዛቤ ለመፍጠር ነው።
በስልጠና መድረኩም ተገኘተው ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጅሀር ሀገሪቱ በሁሉም መስክ እምርታዎ ድሎች ያስመዘገበችበት የትንሳኤ ዘመን ላይ ትገኛለች ብለዋል።
የመደመር ትውልድ የሠላም፣ የአብሮነትና በጋራ የማደግ መንገድ ነዉ ያሉ ሲሆን ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ለሀገራቸዉ ዕድገት የበኩላቸዉን አሻራ የሚያሳርፉበት፣ ለጋራ ጥቅም በጋራ የሚራመዱበት መንገድ በመሆኑ ሀገር ተረካቢ የሆነው ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል እንዲሁም ሴቶች በመደመር እሳቤ በመቃኘት የተመዘገበ ያለውን ልማትና እድገት በማስቀጠል ረገድ የድርሻቸውን መወጣት ይገባል ብለዋል።
የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ ጽ/ቤት ኃላፊ ክብር አቶ ኢብራሂም ይሱፍም በበኩላቸው ብልጽግና ፓርቲ በወጀቦች ሳይበረከክ ያጋጠመውን ችግሮች ወደ እድል በመቀየር ኢትዮጵያን ከተስፋ ብርሃን ወደ ሚጨበጥ ብርሃን ያሸጋገረ ፓርቲ መሆኑን ገልፀው ለዚህም ስኬት መብቃት የወጣቶች እና የሴቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።
ብልጽግና ፓርቲ በ2023 ኢትዮጵያን የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ የሚደረገው ሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞ ከግብ እንዲደርስም ወጣቶች እና ሴቶች የራሳቸውን አሻራ እንዲያኖሩ ሲሉም አጽኖት ሰጥተዋል።
ስልጠናውን የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ ጽ/ቤት ምክትል እና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሻኪር አህመድ የሰጡ ሲሆን በስልጠናው ከተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች መካከል ኢትዮጵያ በ2040 አለም አቀፍ የብልጽግና ተምሳሌት እንድትሆን ለማድረግ ያሉት አስቻይ ሁኔታዎች የመደመር እሳቤ በሀገር ግንባታ ሂደት ሁሉም ተዋኒያን የማይተካ ሚና እንዳላቸው፣ አቅሞችና እሴቶች ተሰባስበውና ተደምረዉ በሀገር ግንባታዉ ሂደት ጉልህ ሚና እንዲጫወቱ መሥራት እንደሚገባ ተዳሷል።
በመድረኩም የመደመር ትውልድ እሳቤ ላይ ትኩረት ያደረጉ የውይይት መነሻ ሃሳቦች ቀርበው ሰፊ ምክከር ተደርጎባቸዋል።
ስልጠናው ለሁለት ተከታታይ ቀናት በሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች የሚሰጥ ይሆናል።


