ድሬዳዋ እና የፈረንሳይዋ ሌጉ ከተማ እህትማማች ከተሞች ሲሆኑ በትምህርት፣ በጤና እና በሌሎችም ማህበራዊ ጉዳዮች አብሮ ለመስራት ስምምነት ተፈራርመዋል።
ታዲያ ልዑክ ቡድኑ ወደ ድሬዳዋ የመጣበት ዋነኛ ምክንያት እህትማማች ከተማነትን ለማጠናከር እንዲሁም በድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ሀሳብ አመንጪነት ልዑክ ቡድኑ በድሬዳዋ ያሉ ምቹ ሁኔታዎችን በመመልከት በተለያዩ ዘርፎች ተሰማርቶ አብሮ ለመስራት በሚቻልባቸው ነጥቦች ላይ ለመምከር ነው።
ልዑኩ በድሬዳዋ ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን፤ ድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ በድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር፣ በድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ በክብርት ወ/ሮ ፈቲያ አደን፣ በድሬዳዋ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ፣ በድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ በክብርት ወ/ሮ ከሪማ አሊ እና በአስተዳደሩ በየደረጃው በሚገኙ አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።


